• Call Us+251 9076 12222
  • Login

NOTICE!!!


ለ8ኛ ክፍል የተማሪ ወላጆች
ጉዳዩ፦ የሚኒስትሪ ፈተና ዝግጅትን ይመለከታል ፣
              እንደሚታወቀው የ8 ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 03 እና 04/2017 ዓ/ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ይሰጣል፡፡ በመሆኑም ለተማሪዎች በመፈተኛ ጣቢያቸው ኦረንቴሽን የሚሰጠው ሐሙስ ፣ግንቦት 28 ስለሆነ ሁሉም ተማሪዎች በዕለቱ በት/ቤት የመገኘት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በፈተናው ሂደት ለሚፈጠር ችግር ት/ቤቱ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን በአክብሮት እያሳሰብን ወላጆች ልጆች ሙሉ የት/ቤት ዩኒፎርም ለብሰው እንዲመጡ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን፡፡ ለተማሪዎች የአድሚሽን ካርድ ስርጭት በዕለቱ የሚከናወን ሲሆን ፈተናው እስኪጠናቀቅ እንዳይበላሽና እንዳይጠፋ ላሚኔት በማስደረግና ከተቻለም የአንገት ላይ ማንጠልጠያ (ባጅ) በማዘጋጀት በአድሚሸን ካርድ መጥፋት ምክንያት ከሚፈጠር መረበሽ ለጆቻችሁን እንድትጠብቁ በዚሁ አጋጣሚ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
በመጨረሻም በፈተና ወቅት ተማሪዎች ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ ሰዓትን ጨምሮ ይዞ መገኘት ከፈተና የሚያሳግድ ተግባር ስለሆነ ከቤት ጀምሮ ክትትል እንድታደርጉ እንጠይቃለን፡፡ ከእርሳስ ፣ ከላፒስና ከመቅረጫ ውጭ ሌላ የጽህፈት መሳሪያ መያዝ የተከለከለ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ከሠላምታ ጋር